Staff

"Please wait"
እባክወ በትዕግስት ይጠብቁ!

በዋድላ ወረዳ የኮን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2017 ዓ .ም የሚሰሩ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ከከተማው ማህበረሰብ ጋር ውይይት አካሄደ።

30-04-2026 20:50pm

በዋድላ ወረዳ የኮን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2017 ዓ .ም የሚሰሩ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ከከተማው ማህበረሰብ ጋር ውይይት አካሄደ። መጋቢት 23/ 2017 ዓ .ም (ዋድላ ኮሙዩኒኬሽን )። በሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ የኮን ከተማ መሪማዘጋጃ ቤት ስለ ከተማዋ መሰረተ ልማት እና መልካም አሰተዳደር ዙሪያ ከከተማው ማህበረሰብ ጋረ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በውይይቱ ላይ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሲልማ ባየ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር አድርገው በመክፈቻ ንግግራቸው ላይም የኮን ከተማን የማልማት ጥያቄን ምላሽ ለመስጠት፣የማዘጋጃ ቤቱን አገልግሎት አሰጣጥ ችግርን ለመፍታት ፣አገልግሎት ስንሰጥ ብልሹ አሰራሮችን ለመቅረፍ ስለሆነ የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰከነ መንፈስ ተረጋግቶ የበስለ ውይይት እንዲአደርግበት በአጽንኦት አሳስበው ውይይቱ በይፋ የተከፈተ መሆኑን አብስረዋል ። መሪ ማዘጋጃ ቤቱ ለውይይቱ ተሳታፊዎች ለማወያያ በመሪ ማዘገጃ ቤቱ ህንጻ ሹም በአቶ ተፈራ ተመስጌን የ8 ወር እቅድ አፈጻጸም፣የገቢታሪፍ ማሻሻል ፣ህገወጥ የቤት ግንባታ ፣የከተማዋ ጽዳትና ውበት ፣መሰረተ ልማትን ማስፋፋት እና ሌሎች የመወያያ አጀንዳዎች በሪፖርት ቀርበው በቀረበው አጀንዳ ላይ የውይይቱ ተሳታፊ የበሰለ ውይይት ተደርጎበታል። የውይይቱ ተሳታፊዎች ለመወያያ አጀንዳ ከቀረበው በተጨማሪ ኮን ከተማን ለማሳደግ ና ለማልማት ብዙ ጥያቄዎችን ናሀሳቦችን በማመንጨት የበሰለ ውይይት ተደርጎል። የኮን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስጋጅ አቶ ተክለ አብ ገላነው እና የዋድላ ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መንጥር ዘሩ የውይይቱ ተሳታፊዎች ያነሷቸው ጥያቂዎች ና ሀሳቦች ትክክል መሆኑን አምነው ያለምንም መሸራረፍ ወስደን እናስተካክላለን ብለዋል። የኮን ከተማ መሪማዘጋጃ ቤት አንዳንድ ባለሞያዎች የቅንነት ችግር ና ሌሎች ብልሹ አሰራርን የሚሰሩትን መረጃ ካገኘን እንዲስተካከሉ እርምጃ አንወስዳለን ሲሉ ማጠቃለያ ሀሳብ ሰጥተዋል።

loading

loading

loading

loading

ይህ መረጃ 15 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----

   ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇    👇    👇   ሚዲያወች በመጫን Share..

Comment Form