የኮን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2015 በከተማዋ ሊያከናውናቸው ያቀዳቸውን የልማት ስራዎች ለኮን ከተማ ነዋሪዎች አቅርቧል።
30-04-2026 21:09pmየኮን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2015 በከተማዋ ሊያከናውናቸው ያቀዳቸውን የልማት ስራዎች ለኮን ከተማ ነዋሪዎች አቅርቧል። በንቅናቄ መድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የዋድላ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ቦያለው ድራሾት "ከጦርነት በኋላ እየመጣ ያለው ከፍተኛ የሆነ የልማት ጥያቄ ነው።የኮን ከተማ አምና ድንቅ የሆነ የመሰረተ ልማት ስራ አከናውኗል። በ2015 ሊሰሩ የታቀዱት እጅግ የሚያማልሉ እቅዶች ናቸው፤ ህዝቡ ከተሳተፈ ፣ ካመነበት በጣም ብዙ ስራወች መስራት እንደምንችል ይታመናል። ስለዚህ ለኮን ከተማ ልማት ሁሉም ሊሳተፍና የበኩሉን ሊወጣ ይገባል።" በለዋል። ማዘጋጃ ቤቱ በከተማዋ ውስጥ በህብረተሰቡ እና በመንግስት በጀት ለማከናወን ያቀዳቸው የመሰረተ ልማት ስራዎች በኮን መሪ ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አራጋው አያሌው ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል። በመድረኩ የተገኙት ተሳታፊዎችም፦"በባለፈው አመት በተሠሩ የመሠረተ ልማት ስራዎች እናመሠግናለን ፣ ማዘጋጃ ቤቱ አሁንም ግለቱን ማሥቀጠል አለበት፣ ገቢ ሠብሳቢወች በየ ቀጠናው ቤትለቤት በመንቀሳቀስ በደረሰኝ ይሰብስቡ ማህበረሰቡ ፊቱን ማዞር የለበትም ገቢ መሥጠት አለበት ፣ማንኛውም የከተማችን ነዋሪ በማዋጣት ከመንግስት ድጋፍ ጋር አካባቢያችንን ማልማት አለበት፣ ሁሉም ህዝብ ተሣታፊ ይሁን አፈፃፀሙ በየ 15 ቀን ይገምገም።" ብለዋል። በተያዘው አመት የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ፣ የውሃ መፋሰሻ ቦይ፣ የጠጠር መንገድና የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ በትኩረት ተይዘው እንደሚሰሩ ተመላክቷል።





